ከባድ ዘመን ላይ ተገኘንና ከባድ ግዜ እያሳለፈን ቢሆንም ክፉም ይሁን መልካም ቀኖች ማለፋቸው አይቀርም እንግዲህ እግዚያብሄር ምህረት አድርጎልን የሠነበትን ሠዎች ከበሽታው ይልቅ ረሀቡ እያንገላታቸው ለሚገኙ ቅድሳን ልንደርስ ይገባል ::ቤተክርስቲያን ትረዳቸው የነበሩ ብቻ ሳይሆን በሠው ቤት ስራ ልብስ አጠባንና ሌሎችንም ስራዎች ሠርተው የእለት ጉርሳቸውን የሚያገኙ በወረርሽኙ ምክንያት ስራቸውን አቁመው ከነቤተሠባቸው ከባድ ፈተና ውስጥ ገብተዋል ከምንበላው እናካፈላቸው በቋሚነት በየወሩ መርዳት የምትፈልጉ ካላቹህ እናገናኛቹሀለን መከራህን እንዳለፈ ውሀ ትረሳዋለህ እንደሚል ቃሉ አልፈን እናየዋለን ሁላችንንም ጌታ ይርዳን (Eden 0912109966)