የተረሳው ችንካር | YETERESAW CHENKAR | ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈሪ | ZEMARIT SISTER HIWOT TEFERI | አዲስ መዝሙር New Orthodox Mezmur | 2024
የተረሳው ችንካር
የባሪያ መልክ ይዘህ ከሰማያት ወርደህ
ለሞት ስትታዘዝ በኛ መስቀል ወጥተህ
ያ ሁሉ መከራህ እኛን መች አመመን
አልገባንም ፍቅርህ ግዴታህ መሰለን ?
ስለኛ የተናከው አንተ የህማም ሰው
እንዲህ የወደድከን ምን አይተህብን ነው
አያመንም እኛን የእግሮችህ ላይ ሳዶር
ቆየን ከረሳነው የእጅህን አላዶር
ይጮኃል ቀን በቀን የመስቀልህን ጣር
ለኛ ግድ ያልሰጠን የተረሳው ችንካር
አዝ ...
ደምህን ስናክፋፋ መንግሥትህን ልንሸጥ
ይገርማል በፍቅርህ ቀን በቀን መገለጥ
እርቃንህን ስትቆም ልትከፍል የኛን እዳ
እኛ መች አየነው ያንተን ከለሜዳ
ይጮሃል ቀን በቀን የመስቀልህን ጣር
ለኛ ግድ ያልሰጠን የተረሳው ችንካር
አዝ ...
አይሁድ ያጠለቁት ያንገትህ ላይ ገመድ
አወጣን ጎትቶ በሲዖል ከመንደድ
ሥጋህን ያነሳው የመከራው ጅራፍ
የፈሰሰው ደምህ ፃፍን በአዲስ ምዕራፍ
ይጮሃል ቀን በቀን የመስቀልህን ጣር
ለኛ ግድ ያልሰጠን የተረሳው ችንካር
አዝ ...
ፊትህ ላይ ሲተፉ ዓይኖችህን አስረው
አንተን የሚታይህ የሰው ልጅ መዳን ነው
ይሄ ሁሉ ፍቅርህ ሳይሞቀን በርዶናል
የአይሁድ እሳት ልንሞቅ ሥራቸው ቆመናል
ይጮኃል ቀን በቀን ያ የመስቀልህ ጣር
ለኛ ግድ ያልሰጠን የተረሳው ችንካር
አዝ ...