ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ተሰቅለ ተሰቅለ | ዘማሪ ዲያቆን ታዬ ብርሃኑ | ዜማ ሰማያት
ዘጎላ ስቱዱዪ | ግጥምና ዜማ መምህር ሲሳይ ወ/አረጋዊ | መሳሪ ተጫዋቾች ዘውዱ ጌታቸው ፣ እንዳልካቸው አዱኛና ኤልያስ ፈቃዱ
ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሉያ አምላክ ተሰቀለ
ሃሌ ሉያ ሕማም ተቀበለ
ሃሌ ሉያ ቤዛ ሊሆን ለዓለም ተሰቀለ መድኃኔ ዓለም
ሞትን ሊዘልፍ ችንካሩን ሊሰብር
ክብሩን ትቶ መጣ ከምድር
ተቀበለ ሕማም በፈቃዱ
የሰውን ልጅ እንዲኹ በመውደዱ
ሃሌ ሉያ ፟==========
ለሱራፌል ዘውድ ያቀዳጃቸው
ለኪሩቤል ግርማ ያለብሳቸው
የሾኽ አክሊል በራሱ አቀዳጁት
ለመዘበት ግምዣን አለበሱት
ሃሌ ሉያ ===========
ሁሉን በእጁ የያዘውን ያዙት
የአምላክን ልጅ አምላክን አሰሩት
ሲጎትቱት የተከተላቸው
እየጠሉት እርሱ ወደዳቸው
ሃሌ ሉያ =========
የፈለገኝ በደሙ ነጠብጣብ
የፈወሰኝ አልቦት የደም ላብ
የደረሰ ነፍሱን እስከ መስጠት
እንዲኽ ዓይነት ፍቅር ማንም የለው በእውነት
ሃሌ ሉያ===========